Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ከ25 ዓመታት በኋላ አምባሳደሯን ወደ ሱዳን ላከች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ከ25 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ አምባሳደሯን ወደ ሱዳን መላኳ ተሰማ፡፡

አሜሪካ ሱዳንን ሽብርተኝነትን ከሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ካወጣች ከሁለት ዓመታት በኋላ ነው የመጀመሪያ አምባሳደሯን ወደ ሱዳን የላከችው፡፡

ይህን ተከትሎም አምባሳደር ጆን ጎፍሬይ በሱዳን ካርቱም መገኘታቸውን በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ሱዳን ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ ከሚባሉት ሀገራት ዝርዝር ውስጥ በፈረንጆቹ 1993 መስፈሯ የሚታወስ ሲሆን ፥ አሜሪካም ካርቱምን አልቃይዳን ትደግፋለች በሚል በዝርዝሩ ውስት አካታት ቆይታለች፡፡

የአልቃይዳ መስራች ኦሳማ ቢን ላደን ከፈረንጆቹ 1992 እስከ 1996 በሱዳን መኖሩ ይነገራል፡፡

በፈረንጆቹ 1997 አሜሪካ በሱዳን ያላትን ውክልና ከአምባሳደርነት ወደ ጉዳይ አስፈጻሚ ደረጃ ዝቅ በማድረግ የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣሏም አይዘነጋም።

ከሁለት አመት በፊትም አሜሪካ በካርቱም ያላትን ውክልና ለማሻሻል መወሰኗን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

ሱዳን በበኩሏ ከ23 ዓመታት በኋላ በአሜሪካ የመጀመሪያ አምባሳደሯን መሾሟም የሚታወስ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.