Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል ም/ ቤት ሁለት ተጨማሪ ወረዳዎች በሲቲ ዞን እንዲቋቋሙ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ሰብሰባ ሁለት ተጨማሪ ወረዳዎች በሲቲ ዞን እንዲቋቋሙ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ።

በሲቲ ዞን ከነበሩት ሰባት ወረዳች በተጨማሪ እንዲቋቋም ለምክር ቤቱ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ እንዳመለከተው በአስቸኳይ ጉባኤው የፀደቁትዱንየር እና ዳይሜድ የተባሉ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በክልል ምክር ቤቱ ቀደም ሲል ስራ ላይ የነበረውን የወረዳና ቀበሌ አደረጃጀት በማሻሻል የክልሉ ወረዳዎች ከ93 ወረዳዎች ወደ 95 እንዲያድጉ የሚያስችለው አዋጅም ቀርቦ ፀድቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.