Fana: At a Speed of Life!

በስንዴ ራሳችንን ከመቻል አልፎ ወደ ውጭ ለመላክ በሚደረገው ሂደት አመራሩና ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በስንዴ ራስን ከመቻል አልፎ ወደ ውጭ ለመላክ በሚደረገው ሂደት አመራሩና ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሶማሌ ክልል ቱሉ ጉሌድ ወረዳ በመገኘት የ2015 የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስራ አስጀምረዋል ።

በመርሃ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ታሪክ የሚቀየረው በልጆቿ ላብ መሆኑን ገልፀው እየለማ ያለው ስንዴ ጥሩ ያልነበረውን የኢትዮጵያና የስንዴ ታሪክ ለውጥ ማሳያ ነው ብለዋል።

በስንዴ ራሳችንን ከመቻል አልፎ ወደ ውጭ ለመላክ በሚደረገው ሂደት አመራሩና ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን በበኩላቸው÷ መስኖ በመጠቀም ከአምናው በእጥፍ ስንዴ ለማምረት ግብ ተጥሎ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለተመዘገበው ውጤትም በየደረጃው ያለው አመራር ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ መሆኑን አስታውሰው በቀጣይም ትብብሩ መቀጠል አለበት ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ÷ በክልሉ ሊታረስ ከሚችለው መሬት እየለማ ያለው 10 በመቶ ወይም 847 ሺህ ሄክታር ብቻ መሆኑን ገልፀው ዘንድሮ ለሚጀመረው የስንዴ ወደ ውጭ መላክ ስራ ክልሉ 2 ሚሊየን ኩንታል እንዲያቀርብ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዚህ አመት በበጋ በሁለት ዙር 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ታለማለች።

ከዚህም 52 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ።
በየአመቱ ለበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ወደ ስራ የሚገባ መሬት በስድስት እጥፍ እያደገ ነው።

በአልዓዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.