Fana: At a Speed of Life!

ለዘላቂ ሰላም አሸባሪው ህወሓት ትጥቅ ይፍታ፤ የሽብር ቡድኑን እስትንፋስ ለማራዘም የሚሠሩ እጆች ይሰብሰቡ- የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዘላቂ ሰላም አሸባሪው ህወሓት ትጥቅ ይፍታ፤ የሽብር ቡድኑን እስትንፋስ ለማራዘም የሚሠሩ እጆች ይሰብሰቡ ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡

በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግን ያልትገባ ጫና የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በደብረብርሃን ከተማ ተካሂዷል፡፡

ሰልፈኞቹ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት ለአሸባሪው ህወሓት የሚያደርጉትን ድጋፍ በማቆም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ ጠይቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚገልጹ መፈክሮችን ይዘው አደባባይ ወጥተዋል።

በሰልፉ ላይም ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ እኛ በቂ ነን ያሉት የሰልፉ ተሳታፊዎ÷ “እናስብላችኋለን” በሚል የሽብር ቡድኖችን በልዩ ልዩ መንገዶች መደገፍ እንዲቆም ጠይቀዋል።

በአላዩ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.