Fana: At a Speed of Life!

የአረፋ በዓል በጋምቤላ እና አሶሳ ከተሞች ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በጋምቤላ እና አሶሳ ከተሞች ተከብሯል፡፡

በዓሉ በርካታ የእስልምና እምነትተከታዮች በተገኙበት ሰላት እና ተክቢራን ጨምሮ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ነው የተከበረው፡፡

በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

በአሶሳ የበዓሉ አከባበር ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን÷ሕብረተሰቡ የአረፋን በዓል ሲያከብር የመረዳዳት ባህሉን ይበልጥ በማጎልበት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ ማህበረሰብ አንድነት እና ሰላም እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸው÷ የክልሉ መንግስት የሕብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.