አገራዊ እሴቶች ለብሔራዊ መግባባት ያላቸውን አበርክቶ የሚዳስስ መድረክ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ እሴቶች ለብሔራዊ መግባባትና ለአገር ግንባታ ያላቸውን አበርክቶ የሚዳስስ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
“አገራዊ እሴቶች ለብሔራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ የሚገኘው መድረክ÷ በሰላም ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ምሁራን እና ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡
መድረኩ ብሔራዊ ማንነት ለአገራዊ አንድነት፣ ብሔራዊ እሴቶች ለአብሮነት እና ብሔራዊ ጥቅም ለአገር ግንባታ የሚኖራቸውን ጠቀሜታ የሚዳስሱ አጀንዳዎች ላይ እንደሚያተኩር ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የብሔራዊ ጥቅም መጠበቅ ለአገር ግንባታ የሚኖረውን ጠቀሜታ በመዳሰስ በመተባበር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በመድረኩ ምክክር እንደሚደረግበት ተመላክቷል።