Fana: At a Speed of Life!

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ17 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጋና ክረምት የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ17 ቢሊየን 644 ሚሊየን 156 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው ሥራዎች መከናወናቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ፣ ደም ልገሳ፣ የመንገድ ትራፊክ ደኅንነትን ጨምሮ በ12 የስምሪት ዓይነቶች የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተካሂዷል።

በሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ መላኩ ባዩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በአገልግሎቱ 24 ሚሊየን 664 ሺህ 225 ወጣቶች ተሳትፈዋል።

በዚህም 56 ሚሊየን 823 ሺህ 452 ወገኖች ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።

በወጣቶቹ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመንግሥትና በሕብረተሰቡ ያልተሸፈኑ ሥራዎችና አገልግሎቶችን መድረስ ስለመቻሉም አመላክተዋል።

እንዲሁም ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በተውጣጡ የወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስኬታማ ሥራ መከናወኑን አስረድተዋል።

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.