Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምሥረታ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምሥረታ ጉባኤ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ተሰማምተው በአንድ ክልል እንዲደራጅ በማለት ድምጻቸውን በሰጡት መሠረት ነው የክልሉ ምስረታ ጉባኤ እየተካሄደ ያለው።

በጉባኤው ላይም የዞኖቹና የልዩ ወረዳዎች አመራሮች ተገኝተዋል።

በጉባኤው ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ መንግስት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ሕገ መንግስቱ ለምክር ቤቱ አባላት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይጸድቃል ተብሏል።
በማቱሣላ ማቴዎስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.