Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልጆች ሰንደቅ አላማችንን በድጋሚ ከፍ አድርገዋል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምንጊዜም ኩራት የሆኑን የኢትዮጵያ ሴት ልጆች ሰንደቅ አላማችንን በድጋሚ ከፍ አድርገዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ትናንት በቡዳፔስት በተካሄደው የሴቶች የ10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር በተገኘው ድል የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷”የምንጊዜም ኩራት የሆኑን የኢትዮጵያ ሴት ልጆች በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ውድድር ላይ ሰንደቅ አላማችንን በድጋሚ ከፍ አድርገዋል” ብለዋል።

በውድድሩ÷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 1ኛ፣ አትሌት ለተሰንበት ግደይ 2ኛ እና አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 3ኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የወርቅ፣ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.