Fana: At a Speed of Life!

የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በተመረጡ አገልግሎት መሥጫ ጣቢያዎች መተግበር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር በልጽጎ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በተመረጡ አገልግሎት መሥጫ ጣቢያዎች ተግባራዊ መሆን ጀመሯል፡፡

የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት የሠራተኛና የሥራ መረጃዎችን በዘመናዊ መንገድ በማስተዳደር ዜጎች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሥራ ዕድሎች ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

በመጀመሪያ ምዕራፍ ሥርዓቱ በአዲስ አበባ ዋናው መሥሪያ ቤት ብቻ ተግባራዊ እየተደረገ መቆይቱን ሚኒስቴሩ በመረጃው አስታውሷል፡፡

በቅርቡም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ የተመረጡ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ሥርዓቱን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

ለተግባራዊነቱ የሚያስፈልጉ የባዮሜትሪክስ፣ የላፕቶፕ፣ የዋይፋይ ራውተርና ሌሎች ቁሳቁሶች ለተመረጡና 400 ለሚሆኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መሥጫ ጣቢያዎች እየተሰራጩ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

አሁን ላይ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ

• በአዲስ አበባ ÷ ቦሌ፣ የካ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ እና ኮልፌ ፤

• በኦሮሚያ ክልል ÷ አምቦ፣ ሻሸመኔ፣ አዳማ፣ አሰላ፣ ቡራዩ፣ ምሥራቅ ሐረርጌ፣ መተሃራ፣ ፉሪ፣ ጉደር እና ጅማ ፤

• በሲዳማ ክልል ÷ ሐዋሳ፣ ባንሳ፣ አለታ ወንዶ እና ወንዶ ገነት ፤

• በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ÷ በቴፒና በሌሎች ከተማ በሚገኙ የተወሰኑ ማዕከላት አገልግሎት መሥጠት ተጀምሯልም ነው የተባለው።

የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር በሀገር ውስጥና በውጭ ሃገር በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ ባስተላለፈው የምዝገባ ጥሪ መሰረት ከ180 ሺህ በላይ ዜጎች በድረ-ገጽ ተመዝግበው የባዮሜትሪክስ ምዝገባ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙም ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.