Fana: At a Speed of Life!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ጠቅላይ መምሪያ እየተሠራ ያለውን  የሕግ ማስከበር ሥራ ገመገመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ጠቅላይ መምሪያ የአማራ ክልልን ወደ ሰላም ለመመለስ እየተሠራ ያለውን  የሕግ ማስከበር ሥራ ገምግሟል።

የኮማንድ ፖስት ከፍተኛ አመራሮች አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ ጀኔራል አበባው ታደሰ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ፣ የመከላከያ ከፍተኛ ጀኔራል መኮንኖች እና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው ግምገማው የተካሄደው፡፡

በግምገማውም÷ ክልሉ ከነበረበት የጸጥታ ችግር እየተላቀቀ ወደ ተሟላ ሰላም ለመመለስ እየተከናወነ ያለው ሕግ የማስከበር ሥራ ውጤታማ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

በክልሉ ያለው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴም መሻሻል ማሳየቱ በግምገማው መነሳቱን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በቀጣይ የተጀመረውን ሕግ የማስከበር ሥራ በውጤታማነት በማጠናቀቅ ክልሉን ወደ ተሟላ ልማት እንዲገባ እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ መምሪያው አስታውቋል።

ሕብረተሰቡ የሕግ ማስከበር ሥራው እንዲሳካ ላሳየው ሁሉ-አቀፍ ድጋፍ ጠቅላይ መምሪያው አመስግኗል፡፡

በቀጣይም ሕብረተሰቡ በየደረጃው ካለው የሕግ አስከባሪ እና የኮማንድ ፖስት አመራር ጋር በመሥራት የተለመደ አስተዋጽኦውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠቅላይ መምሪያውጠይቋል፡፡

ግምገማው የተካሄደው የኮማንድ ፖስቱ ከፍተኛ አመራሮች የጎርጎራ ፕሮጀክትን ከጎበኙ በኋላ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.