Fana: At a Speed of Life!

18ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ የ18ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል መነሻ እቅድ ላይ ተወያይቷል፡፡

በዓሉ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በሶማሌ ክልል አስተናጋጅነት በጅግጅጋ ከተማ ‘ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት’ በሚል መሪ ቃል በድምቀት ይከበራል መባሉን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስብሰባውን የመሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር÷ በዓሉ የሕዝቦችን ሕብረ ብሔራዊ አንድነትና ትስስር በማጠናከርና በሕገ መንግሥቱና በፌዴራል ስርዓቱ ላይ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ ተናግረዋል፡፡

በበዓሉ ላይ ለፍትሕ፣ ለእኩልነት፣ ለነፃነትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መሠረት የሚሆኑ ውይይቶችና ምክክሮች እንደሚካሄዱም ጠቁመዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.