Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌዳሞ ከዩ ኤስ ኤይድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የረድዔት ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) በኢትዮጵያ ዳይሬክተር ስኮት ሆክላንደር የተመራ ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በውይይታቸውም በክልሉ በድርጅቱ ድጋፍ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አቶ ደስታ አብራርተዋል፡፡

ድርጅቱ ወጣቶችን መሰረት አድርጎ እየሠራቸው ባሉ ጉዳዮች ላይም መምከራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያላክታል፡፡

በቀጣይ በክልሉ ትኩረት በሚደረግባቸው ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አራርሰው ገረመው (ዶ/ር)÷ ለክልሉ ልማት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ለአብነትም በክልሉ በ ዩ ኤስ ኤይድ ድጋፍ ሰባት ፕሮጀክት እየተተገበሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.