44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ይነሱበታል ተብሎ የሚጠበቀው 44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል፡፡
በጉባኤው ለ37ኛው የመሪዎች ጉባኤ አጀንዳ ማርቀቅን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች እንደሚነሱበት የህብረቱ መርሐ-ግብር ያሳያል።
ኢትዮጵያ አጋጣሚውን ለፖለቲካዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና ዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች ለመጠቀም ዝግጅት ማጠናቀቋን የተናገሩት ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ናቸው።
በጉባዔው ከአፍሪካ ሀገራት በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ሌሎች ሀገራት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
እንዲህ ዓይነት ጉባኤዎች ለአስተናጋጅ ሀገራት የኮንፈረንስ ቱሪዝም በረከታቸው የላቀ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
በአፈወርቅ እያዩ
#Ethiopia #AU #AddisAbeba
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!