Fana: At a Speed of Life!

በጅግጅጋ የተገነባው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አማካኝነት በጅግጅጋ ከተማ የተገነባው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጥቂት ወራት በፊት በጅግጅጋ ከተማ የማዕከሉን ግንባታ ማስጀመራቸው ይታወሳል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቅቆ ትናንት በከተማዋ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድም÷ ከንቲባ አዳነች በአዲስ አበባ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ተጠቃሚ እያደረገ ያለውን ተግባር በማስፋት በጅግጅጋ ከተማ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል እንዲገነባ በማድረጋቸው አመስግነዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.