የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ።
በጉባዔው የክልሉ መንግሥት ያለፉት ስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የጠቅላይ ኦዲት መስሪያቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥራ ዕቅድ ክንውኖችን ጨምሮ ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።