Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከሞሪታንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሞሪታንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ኡልድ ጋዙዋኒ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዛሬ ማለዳ ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

በውይይታቸውም በየሀገራችን ያሉ ጉዳዮችን ብሎም አኅጉራዊ ጉዳዮችን አንስተን መክረናል ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ኡልድ ጋዙዋኒ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ሆነው ሥራ በመጀመራቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.