Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊ መሪዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ መሪዎች እና የልዑካን ቡድን አባላት ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው።

በዚህ መሰረትም የጋና፣ የብሩንዲ ፣ የዚምባቡዌ ፣የኮሞሮስ ፣ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ የደቡብ ሱዳን እና የሲሸልስ መሪዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ 49 ሀገራት ተሳትፈዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 30 የሀገራት ፕሬዚዳንቶችና ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንዲሁም ስድስት ምክትል ፕሬዚዳቶች እንደሚገኙበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.