Fana: At a Speed of Life!

ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉት የኮሪደር ልማት መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ ማቆም ተከለከለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሪደር ልማት ስራዎቻቸው ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ከአምስቱ የኮሪደር ልማት ስራዎች ውስጥ ከአራት ኪሎ እስከ ቅ/ማሪያም ቤ/ክርስቲያን መታጠፊያና ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ መሐሙድ ሙዚቃ ቤት በትናንትናው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው ያታወቀል፡፡

በተጨማሪም ከቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም በደጎል አደባባይ እስከ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን አቅጣጫ መንገዱ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

ስለሆነም በህጋዊ የመንገድ ተጠቃሚነት ራስንና ሌሎችን ከመንገድ ትራፊክ አደጋ ስጋት በመጠበቅና ለመንገድ መሰረተ ልማቶች ተገቢውን እንክብካቤና ጥበቃ ማድረግ የእያንዳዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆኑን ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉት መንገዶች ላይ ተሸከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.