አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሌሎቸ ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ውይይቱ በሩሲያ እየተካሄደ ከሚገኘው የብሪክስ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡