የጨፌ ኦሮሚያ አባላት የችግኝ ተከላ አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጨፌ ኦሮሚያ አባላት በአዳማ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አከናውነዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱራህማንን ጨምሮ የጨፌው አባላት ተሳትፈዋል።
አፈጉባዔ ሰዓዳ የኦሮሞ ህዝብ ለእፅዋትና ደን ትልቅ ቦታና ጥብቅ ትስስር አለው ብለዋል።
የተከለውን መንከባከብና መጠበቅ ደግሞ አብሮት የኖረ ዕሴቱ ነው ብለዋል።
አፈ ጉባዔዋ የጨፌ አባላቱ መትከል ብቻ ሳይሆን እንዲፀድቁ እንክብካቤ የሚያደርጉ መሆኑን ገልፀዋል።
በመራኦል ከድር