Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የተከሰተው የመሬት መንሸራተት ባደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ሕይወት ላይ ባደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

በወረዳው ትናንት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሥድስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በተጨማሪ ሥድስት ወገኖች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

ይህን ተከትሎም ርዕሰ መሥተዳድሩ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት÷ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችን አጽናንተው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም ቶሎ እንዲያገግሙ ተመኝተዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት ተገቢው ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው÷ በሌሎች አካባቢዎች መሰል ችግሮች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ሕብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.