Fana: At a Speed of Life!

የገቢ አሰባሰቡን ለማሳደግ የተቀናጀ ሕግ የማስከበር ሥራ ወሳኝ ነው- ሚኒስቴሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተረጋጋ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለመፍጠርና የገቢ አሰባሰቡን ለማሳደግ ወጥነት ያለው የተቀናጀ ሕግ የማስከበር ሥራ ወሳኝ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ አስገነዘቡ፡፡

የ2016 በጀት ዓመት የኮንትሮባንድ፣ የታክስና የንግድ ማጭበርበር መከላከልና መቆጣጠር ሥራዎች አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ሚኒስትሯ በመድረኩ ላይ ባለፉት ዓመታት የፍትሕና የፀጥታ ተቋማት የተሻለ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸው÷ በተያዘው የበጀት ዓመትም ይህን አበረታች ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በተከናወኑ ሥራዎችም የሀገር ሀብትን ከሌቦች ማዳን ተችሏል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በመድረኩ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የፍትሕ ሚኒስቴር አመራሮች እየተሳተፉ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.