በሐረሪ ክልል የተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ ነው
አዲስ አበበ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ መሆኑን የሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ምዝገባው በክልሉ በገጠር እና ከተማ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡
ወላጆችም ለትምህርት የደረሱ ልጆቻቸውን በንቃት እንዲያስመዘግቡ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡