በተለያዩ ክልሎች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በተለያዩ ክልሎች እየተከበረ ነው፡፡
በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሐሳብ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ እየተከበረ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በክልል ደረጃ የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል እየተከበረ ነው፡፡
የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ መቱ አኮ እንዳሉት÷ የቀኑ መከበር ዋና ዓላማ ክልላዊና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት እንዲዳብር ማስቻል ነው።
እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሆሞሻ ወረዳ 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በተለያዪ ዝግጅቶች እየተከበረ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ሕዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚከበር ይታወቃል ።
በተስፋዬ ምሬሳ