Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል ግምታዊ ዋጋው 14 ሚሊየን ብር የሆነ የኮንትሮባንድ እቃ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል ግምታዊ ዋጋው 14 ሚሊየን ብር የሆነ የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ጣሰው ቻለው ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለፁት÷ የኮንትሮባንድ እቃው የተያዘው ፖሊስ ባደረገው የተጠናከረ ክትትል ነው።

የኮንትሮባንድ እቃው የተያዘው በኮድ 3 ታርጋ ቁጥር 06153 ድሬ በሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ መሆኑን ጠቁመው÷ እቃው ከነተሽከርካሪው መያዙን አስረድተዋል።

የተያዘው የኮንትሮባንድ እቃ በዋናነት ሲጋራና ሌሎች ቁሳቁሶችን ያካተተ መሆኑነም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡ እና ፖሊስ ያደረጉት ቅንጅት ለኮንትሮባንድ ዕቃው መያዝ ትልድ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው፤ ህብረተሰቡ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

በተስፋዬ ሀይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.