Fana: At a Speed of Life!

የተሃድሶ ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ ታጣቂዎች የጎንደር ከተማ ልማትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተሃድሶ ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ ታጣቂዎች በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ስልጣኞች የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስት ዓለም አቀፍ ቅርስ እድሳት እንዲሁም በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ሰልጣኞቹ በአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ በጊዜያዊ የተሃድሶ ስልጠና ማዕከል ሲሰለጥኑ የቆዩ መሆናቸውን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.