Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ5 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ያስመዘገቡ ኢንቨስተሮች የማዕድን ዘርፍ ፈቃድ ወሰዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ 5 ቢሊየን 409 ሚሊየን 611 ሺህ 136 ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ኢንቨስተሮች በማዕድን ዘርፍ ፈቃድ መውሰዳቸውን የአማራ ክልል ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

4 ቢሊየን 275 ሚሊየን 189 ሺህ 229 ብር ካፒታል ላስመዘገቡ ኢንቨስተሮች ፈቃድ ለመሥጠት ያቀደው ቢሮው÷ ከዕቅድ በላይ መፈጸም መቻሉን አስታውቋል።

አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ65 ነጥብ 8 በመቶ ብልጫ ማሳየቱንም ገልጿል።

በግማሽ ዓመቱ በማዕድን ዘርፉ ከሚሰማሩ ባለሃብቶች፣ ኩባንያዎች እና ኢንተርፕራይዞች 12 ሺህ 889 የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም ለፋና ዲጂታል አረጋግጧል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር የ22 ነጥብ 11 በመቶ ብላጫ ማሳየቱን ነው ያመላከተው፡፡

በበጀት ዓመቱ 8 ቢሊየን 550 ሚሊየን 378 ሺህ 457 ብር ካፒታል ለሚያስመዘግቡ ኢንቨስተሮች ፈቃድ ለመስጠት ማቀዱንም ቢሮው ጠቁሟል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.