በጎ ፈቃደኛ የትራፊክ አስተባባሪ ወጣቶች የሚለብሱት አንጸባራቂ ሰደርያ ቀለም ተቀየረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ሥር የሚገኙ የበጎ ፈቃደኛ ትራፊክ አስተባባሪ ወጣቶች አገልግሎት ሲሰጡ የሚለብሱት አንጸባራቂ ሰደርያ ቀለም ተቀየረ፡፡
አሁን አገልግሎት ላይ የዋለው አንጸባራቂ ሰደርያ ቀለም ደማቅ ብርቱካናማ መሆኑን ባለስልጣኑ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባጋራው መረጃ እወቁልኝ ብሏል፡፡
ይህን ተከትሎም የቀድሞው አንጸባራቂ ሰደርያ አገልግሎት ላይ አንደማይውል አረጋግጧል፡፡