Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከተኪ ምርት ከ332 ሚሊየን ዶላር በላይ ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ሰባት ወራት ከተኪ ምርቶች ከ332 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማዳን መቻሉን የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ያለፉትን ሰባት ወራት የሥራ አፈጻጸም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደብረ ብርሃን ከተማ እየገመገመ ነው፡፡

በበጀት ዓመቱ 111 ኢንዱስትሪዎች በአዲስ መልክ ሥራ መጀመራቸውን የቢሮው ኃላፊ እንድሪስ አብዱ በመድረኩ ላይ አንስተዋል፡፡

242 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 1 ሺህ 354 አዳዲስ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ጥያቄ ማቅረባቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ባለፉት ሰባት ወራት 39 ኢንዱስትሪዎችና አራት የአበባ አምራቾች 67 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማስገኘታቸውንም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በ430 አምራች ኢንዱስትሪዎች አማካኝነት ከ258 ሺህ ቶን በላይ ተኪ ምርቶችን በማምረት ከ332 ሚሊየን ዶላር የሚልቅ የውጭ ምንዛሪ ማዳን መቻሉን ነው ያነሱት፡፡

በኤልያስ ሹምዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.