Fana: At a Speed of Life!

በ120 ሚሊየን ብር እየተገነቡ ካሉ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች መካከል ሥድስቱ ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል ገጠር ወረዳ በ120 ሚሊየን ብር እየተገነቡ ከሚገኙ 14 የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች መካከል ሥድስቱ ለአገልግሎት በቁ፡፡

የውኃ ፕሮጀክቱን ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ናቸው።

በኤረር እና ሶፊ ወረዳ የተገነቡት የውኃ ፕሮጀክቶች የውኃ ማጠራቀሚያ ታንከር፣ የውኃ መቅጃ ቦኖዎች፣ የኤሌክትሪክና የሶላር ኃይል አቅርቦትና ሌሎች ግንባታዎች እንደተከናወነላቸው የክልሉ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ሥራ አስኪያጅ ዲኔ ረመዳን ተናግረዋል፡፡

የፕሮጀክቶቹን ለአገልግሎት ክፍት መሆን ተከትሎም የክልሉ የገጠር የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋን 66 በመቶ ደርሷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.