Fana: At a Speed of Life!

በማሕበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን እንቦጭ አረምን የማስወገድ ሥራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንቦጭ አረምን ለማስወገድ ያለመ ማኅበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደምቢያ፣ ምሥራቅ ደምቢያ፣ ጎንደር ዙሪያ እና ጣቁሳ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች ተጀመረ፡፡

በንቅናቄው እየተሳተፉ ያሉ የአካባቢዎቹ  ነዋሪዎች እንዳሉት፤ ጣና ሐይቅ የሕይወታችን መሠረት ነው፤  እንቦጭ አረምን ከሐይቁ ለማስወገድ በቅንጅት እንሠራለን፡፡

የዞኑ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፤ የጣና ሐይቅን ኅልውና ለመጠበቅ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

በዚህም በጣና ሐይቅ አዋሳኝ ወረዳዎች የማሕበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ በመፍጠር በተከናወነ ሥራ፤ በ767 ሔክታር ላይ የእንቦጭ አረም ማስወገድ ተችሏል ማለቱን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ንቅናቄው ለሚቀጥሉት 25 ቀናት በአራት ወረዳዎች እና 18 ቀበሌዎች የሚቀጥል ሲሆን፤ በዚሁ ሥራ ከ30 ሺህ 592 በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.