አፍሪካ በኢኮኖሚ መስክ ጠንካራና ልዑላዊነቷን ያስከበረች እንድትሆን የያዘችውን ጥረት ማጠናከር ይገባል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አፍሪካ ከፖለቲካ ነፃነት ባሻገር በኢኮኖሚም መስክ ጠንካራና ልዑላዊነቷን ያስከበረች እንድትሆን የያዘችውን ጥረት ማጠናከር ይገባናል አሉ በአኅጉሪቱ በኢኮኖሚ ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ባለድርሻ አካላት።
የዘርፉ ተዋንያን በናይጄሪያ አቡጃ ከተማ በተጀመረው የአፍሪካ ኤክስፖርት ኢምፖርት (አፍሪኤግዚም) ባንክ 32ኛው ዓመታዊ ጉባዔ ላይ÷ አፍሪካውያን በራሳችን ጥረትና እንቅስቃሴ የኢኮኖሚ ነጻነታችንን ለመጎናፀፍ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ዓለም እየገጠማት ካለው የማይተነበዩ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን ለመቋቋም በግልና በጋራ ተቀናጅቶ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ ያመለከቱት የኢኮኖሚ ዘርፍ ባለሙያዎች÷ ይህንን የሚመጥን ጥረት ማድረግ ይገባልም ነው ያሉት።
የቀድሞው የዚምባብዌ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ፓትሪክ ቺማናሳ ሀገራቸው በሌሎች ኃይሎች ተጽዕኖ ኢኮኖሚዋ ተጎድቶ በነበረበት ወቅት አፍሪካውያን የፋይናንስ ተቋማት ባደረጉላት እገዛና በራሷ ጥረት አሁን በተሻለ አቅም ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል።
የዋይቲኬር ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሮዛ ዋይቲኬር በበኩላቸው÷ አፍሪካ ውስጥ ባለፉት ሦስት አስርት የተከናወኑ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች አህጉሪቱ በፋይናንስ ዘርፍ የተሻለ አቅምና ብቃት እንዳላት የሚያመላክት ነው ብለዋል።
በዚህም ረገድ ባንኩ ያሳየው ጅምር አፍሪካን ሞዴል የሚያደርጋት እንደሆነ የባንኩ መረጃ አመላክቷል።
ባንኩ ባለፉት ዓመታት ያደረገው ጥረትና ያስመዘገበው ውጤት አፍሪካ በኢኮኖሚው መስክ ራሷን ችላ ልትቆም እንደምትችል አሳይቷል ያሉት ደግሞ ቫሊዩ ፓርትነር ኤሺያ ድርጅት ተወካዩ ኪ ቾንግ ሊ ናቸው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!