Fana: At a Speed of Life!

በሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ የሕብረተሰብ ተሳትፎ እንዲኖር ወጣቶች ሚናቸውን እየተጫወቱ ነው – መስፍን አርአያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ የሕብረተሰብ ተሳትፎ እንዲኖር ወጣቶች የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ ናቸው አሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር)።

“የወጣቶች ሚና ለውጤታማ ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሐሳብ ከወጣቶች ጋር የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት÷ ተሻጋሪ ለሆኑ ችግሮች እና አለመግባባቶች መፍትሄ ለመስጠት ኮሚሽኑ እየተገበረ የሚገኘው የውይይት እሳቤ እንዲሳካ የላቀ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝነት እንዳለው ተናግረዋል።

በዚህም ወጣቶች በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱ ያላሰለሰ ጥረትና ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አንስተዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ባደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ ወጣቶች ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ አጀንዳዎችን የመለየት ስራን በመስራት ረገድ የወጣቶች ሚና የጎላ እንደነበርም አመላክተዋል።

ወጣቶች በተለያየ የጊዜ ልዩነት በሚከሰቱ ግጭቶች ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ መሆናቸውን ያነሱት ዋና ኮሚሽነሩ÷ ይህንንም ታሪክ በመቀየር ወጣቶች ለሰላምና መረጋጋት መስፈን ግንባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን የበኩላቸውን ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

አለመግባባቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲሁም ግጭቶች በውይይት እንዲፈቱ የማድረግ ታላቅ ሀገራዊ ግብ ይዞ እየተንቀሳቀሰ በሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ተሳታፊ ያልሆኑ ወጣቶች እንዲሳተፉም ተጠይቋል።

ሔብሮን ዋልታው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.