በሀረሪ ክልል የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር እየተሰራ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር እየተሰራ ነው አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።
ርዕሰ መስተዳድሩና ካቢኔያቸው የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማስጀመር እየተሰራ የሚገኘውን ሕንጻ ተመልክተዋል።
አቶ ኦርዲን በድሪ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ማዕከሉ በተለይም ከአገልግሎት ጋር በተያያዘ በተቋማት የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታት ረገድ ጉልህ ፋይዳ ያበረክታል።
የማዕከሉ አገልግሎት ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን በማስቀረት ህዝቡ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላልም ነው ያሉት።
በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተስፋዬ ኃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!