በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 440 ሺህ 656 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፈነ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመኸር እርሻ 440 ሺህ 656 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በዓመታዊ ሰብል 489 ሺህ 578 ሄክታር መሬት ለመሸፈን ታቅዶ 498 ሺህ 528 ሄክታር መሬት ታርሷል።
ይህም ከዕቅድ በላይ መፈጸሙን እንደሚያሳይና ከዚህ ውስጥ 440 ሺህ 656 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ተናግረዋል።
እስካሁን ከተዘሩ ዋና ዋና ሰብሎች መካከልም ስንዴ፣ ጤፍ፣ ገብስ፣ በቄላ፣ አተር፣ ቦሎቄ ሰብሎች እንዲሁም አትክልት እና ሥራሥር ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በክልሉ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማዘመን የግብርናን ምርታማነት እና የተመጣጠነ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ግብ በማስቀመጥ እየተሰራ መሆኑንም የተናገሩት።
በእርሻው ወቅት 275 ትራክተር ለግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት መዋሉን አንስተው÷ ሌሎች የምርታማነት ማሳደጊያ ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች በበቂ ሁኔታ መቅረቡን አስረድተዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!