ኢቢሲ በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
በዲጂታል ኢቢሲ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አትሌቶች፣ አርቲስቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የኢቢሲ ዲጂታል አሠራርና የይዘት ስብጥር የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው።
ኢቢሲ መረጃን በተለያዩ አማራጮች የሁሉንም መልክ በሚያሳይ መንገድ ተደራሽ ማድረጉ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን አርአያ እንደሚሆን አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ መረጃ ለሚዲያ ዘርፍ ካስማ በመሆኑ በሰው ሰራሽ አስተውሎት መታገዝ እንዳለበት አስረድተዋል፡፡
ተመልካችና አድማጭ የተለያየ የመረጃ ፍላጎት እንዳላቸው የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ÷ የኢቢሲ መተግበሪያ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም በተመልካች የመረጃ ፍላጎት መሰረት መረጃን ማቀበል የሚያስችል እንደሆነ አንስተዋል።
የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ÷ ኢቢሲ ያሉትን ሁሉንም የይዘት አማራጮች በዲጂታል መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች አከናውኗል ብለዋል።
በተለይ ሁሉንም የይዘት አማራጮች ከዶትስትሪም የማኅበራዊ ሚዲያዎቹ ጋር አንድ ላይ የሚገኝበት የሞባይል መተግበሪያ የኢቢሲን ዲጂታል መንገድ እንደሚያሳድግ አመልክተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!