Fana: At a Speed of Life!

የሕገ ወጡ ህወሓት ሴራ ሳይስፋፋ ብትንትኑ እንዲወጣ ተደርጓል – አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕገ ወጡ ህወሓት ሴራ ሳይስፋፋ ብትንትኑ እንዲወጣ ተደርጓል አሉ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀ መንበር አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)::
የትግራይ ህዝብ ስር የሰደደ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ያለው መሆኑን የተናገሩት ሊቀመንበሩ ህዝቡ ለሀገሩ እና ለአንድነቱ ቀናኢ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እንድትፈርስ የሚፈልጉ እንደ ግብፅ ያሉ የቆዩ ጠላቶች እና የግብፅ ተባባሪ የሆነው የሻዕቢያ ኃይል ከህወሓት አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የጥፋት ስብስብ አቋቁመው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
የጥፋት ተልዕኮ ያነገበው ሕገወጡ ቡድን ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶች እና ከሀገር ውስጥ ተላላኪዎች ጋር የተመሰረተ ሴራ መሆኑን ያነሱት ሊቀ መንበሩ የህወሓት አመራር የነዚህ ኃይሎች ወኪል በመሆን ስብስቡ እንዲፈጠር ማስተባበሩን አንስተዋል፡፡
መቐለ ላይ አዋጅ በማወጅ ለመንቀሳቀስ አቅደው እንደነበረም አብራርተው ነገር ግን ይህ አደገኛ እቅድ በፍጥነት ተነቅቶበት፣ ሴራው ሳይስፋፋ ብትንትኑ እንዲወጣ ተደርጓል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.