Fana: At a Speed of Life!

በበጀት አመቱ 343 ሺህ ከረጢት ደም ለመሰብሰብ ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ ደም ባንክ በተያዘው ዓመት 343 ሺህ ከረጢት ደም ለመሰብሰብ ማቀዱን አስታወቀ።
የብሔራዊ ደም ባንክ ዋና ዳሬክተር አቶ ያረጋል ባንቴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ በ2012 ዓ.ም ባንኩ በታሪኩ ከፍተኛውን ደም የሰበሰበበት እንደነበር ገልፀዋል።
በዚህም 288 ሺህ ከረጢት ደም እንደሰበሰበ በመግለፅ 112 ሺህ ከረጢት ደሙ ከአዲስ አበባ መሰብሰቡን አስታውቀዋል።
የህብረተሰቡ ደም የመለገስ ግንዛቤ እየጨመረ መምጣት ለዚህ ምክንያተ መሆኑንም ተናግረዋል።
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከሆስፒታሎች የሚቀርበው የደም ፍላጎት አነስተኛ እንደነበር ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል ሆስፒታሎች ከደም ባንክ የወሰዱትን ደም ለምን እንደተጠቀሙበት ሪፖርት እንደማያደርጉ እና በህክምና ስህተት የሚያልፈውን የሰው ህይወት በደም እጥረት እንደሆነ በማስመሰል ሪፖርት የሚያደርጉ ሆስፒታሎች እንዳሉም ጠቅሰዋል።
አንዳንድ የግል ሆስፒታሎች በነጻ የተለገሰን ደም በክፍያ እንደሚሸጡ እና ይህ ደግሞ ትልቅ ስህተት መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
ደም አይሽጥም አይለውጥም ህብረተሰቡ እንደዚህ ዓይነት ችግር ሲጋጥመው ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
በሲሳይ ጌትነት
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.