የህወሓት የጥፋት ቡድን ያሰለጠናቸዉ የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖች ሲጠቀሙበት የነበረ የጦር መሳሪያ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ህዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት የጥፋት ቡድን ያሰለጠናቸዉ የኤርትራ ተቃዋሚ ቡድኖች ሲጠቀሙበት የነበረ የጦር መሳሪያ በሁመራ ከተማ ተያዘ፡፡
የተያዙት የጦር መሳሪያዎች የኢትዮጵያንና ኤርትራ መንግስትን ለመቃወም የህወሓት የጥፋት ቡድን ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ቡድኖች ሲጠቀሙ የነበሩባቸው የተለያዩና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ መሆናቸውን ከመተማ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ፣ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ፖሊስ እና የአካባቢዉ ሚሊሻ በወሰዱት ህግ የማስከበር ተግባር የጦር መሳሪያዎቹ መያዛቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰዉ ተናግረዋል፡፡