ጁንታው ለህፃናት አደንዛዥ እፅ በመስጠት ለሞት እየዳረጋቸው ነው – እጁን ለመከላከያ የሰጠ ህፃን
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድን ህፃናትን በማስገደድ ወደ ጦር ሜዳ ከወሰደ በኋላ አደንዛዥ እፅ በመስጠት ለሞት እየዳረጋቸው መሆኑን እጁን ለመከላከያ የሰጠ ህፃን አጋልጧል።
የ13 አመቱ ህፃን ግርማይ ብሩ እናትና አባቱ መሞታቸውን ተከትሎ በጎዳና ነበር የሚኖረው።
አሸባሪው ቡድንም ህጻን ግርማይን ከጎዳና አንስቶ ወደ ጦር ሜዳ ያስገባው ሲሆን÷ በአጭር ስልጠና የጦር መሳሪያም አስታጥቆታል።
“ሀሽሽ በነጭ ወረቀት ጠቅልለው ይሰጡን ነበር፣ አዲስ አበባ ገብተን ስልጣንም እንይዛለን ብለው ያባብሉናል” ሲል ይገልጻል።
አብረውት ፊሊሞን፣ ሀጎስና ዳንኤል የሚባሉ ህፃናትን ጨምሮ 24 ህፃናት መሞታቸውን እሱም ለመከላከያ እጁን መስጠቱን አስረድቷል።
“አድጌ መማር ዓላማዬ ቢሆንም ባልገባኝ ጦርነት ተሰቃይቻለሁ ” ያለው ግርማይ÷ “መከላከያና አማራን ግደሉ፣ ከያዟችሁ አይለቋችሁም” ብለው ሲነግሯቸው መቆየታቸውን ተናግሯል።
እጁን ከሰጠ በኋላ ግን ከመከላከያ ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑን ገልጾ÷ ሌሎችም በጁንታው ፕሮፖጋንዳ እንዳይታለሉ ጠይቋል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!