Fana: At a Speed of Life!

የሺኒሌ ነዋሪዎች ነገ ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል የሺኒሌ ከተማ ነዋሪዎች ነገ ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዝግጁ መሆናቸው ገለፁ።
ነዎሪዎቹ በነገው ዕለት በክልሉ የሚካሄደው ምርጫ ለቀጣዩ 5 ዓመት ይመራናል ብለን የምናስበውን መንግስት ለመመስረት የሚያስችሉ እጩዎችን ለመምረጥ የተዘጋጀንበት ነው ብለዋል።
ሁሉም ማህበረሰብ በሰላምና በነፃነት ወጥቶ ድምፁን ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ሊሠጥ እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡
ማህበረሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲሁም ከምርጫ አስፈፃሚዎች ጋር በመቀናጀት የነገው ምርጫ ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩሉን ሚና እንዲወጣም መልክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል የሶማሌ ክልል ብዙኃን መገናኘ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.