Fana: At a Speed of Life!

ነገ አዲሱ የሲዳማ ክልል መንግስት ይመሠረታል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መስከረም 20 በሚካሄደው ጉባኤ አዲሱ የሲዳማ ክልል መንግስት እንደሚመሰረት የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ሰለሞን ላሌ ገለጹ፡፡
ዛሬ 190 የምክር ቤት አባላት እንደሚሸኙም ገልፀው÷ ምክር ቤቱም ባለፉት አመታት በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡
የሲዳማ ክልል 5ኛው ዙር ምርጫ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የምክር ቤት አባላት የሽኝት ዝግጅት በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የምክር ቤቱ አባላት በቆይታቸው በርካታ ተግባራትን ማከናወናቸውን ገልፀው÷ በቀጣይ በተቻላቸው አቅም ህዝባቸውን እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል፡፡
በምክር ቤቱ አዲስ የሚመረጡ የምክር ቤት አባላት ሀገርን ሊያሻግር የሚችል ስራን ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ እምነት እንዳላቸውም ነው ያነሱት፡፡
የሲዳማ ክልል ምክርቤት ነገ መስከረም 20 /2014 በሚያካሄደው ጉባኤ አዲሱ የሲዳማ ክልል መንግስትን የሚመሰረት ሲሆን÷ በእለቱም አዳዲስ የምክር ቤት አባላትን የመምረጥና የመተካት ሒደት ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.