Fana: At a Speed of Life!

ሕዝብ የሚሰጠንን ድምጽ በፀጋ እንቀበላለን – የተፎካካሪ ፓርቲዎች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝብ የሚሰጠንን ድምጽ በፀጋ እንቀበላለን በሀረሪ ክልል እየተካሄደ ባለው 6ኛው ሀገር አቀፍ እየተወዳደሩ የሚገኙ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፖርቲ አመራሮች ገለጹ፡፡

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሃረሪ ክልል እየተካሄደ ነው፡፡

የምርጫው ሂደት ገለልተኛና ፍትሃዊ ሆኖ እየተካሄደ በመሆኑ በክልሉ ምርጫ እየተሳተፉ የሚገኙ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።

የፖርቲዎቹ አመራሮች ምርጫው በሠላም እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው÷ ሕዝብ የሚሰጠንን ድምጽ በፀጋ እንቀበላለንም ብለዋል።

ዛሬ ከማለዳው አንስቶ ምርጫው ያለ አንዳች የጸጥታ ችግር እና ስጋት ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

በምርጫው እየተሳተፈ የሚገኘው የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ የሀረሪ ክልል ሊቀ መንበር እና የሀረሪ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ መሀመድ ሃሰን እንዳሉት÷ ምርጫው በክልሉ በተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች እስከአሁን በሰላም እና ህዝቡም በነፃነት ለፈለገው ፓርቲ ድምፁን እየሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

ፓርቲያቸው ያሰማራቸው ታዛቢዎችም ምርጫውን በነጻነት በመታዘብ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ፓርቲዎችም የህዝብን ድምፅ በጸጋ መቀበል እንደሚኖርባቸው አሳስበው ፓርቲያቸውም ይህንኑ በተግባር ለማሳየት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በሀሪሪ ክልል ዛሬ እየተካሄደ ባለዉ የህዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤት ምርጫ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተፎካከሩ ይገኛሉ።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.