Fana: At a Speed of Life!

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ 6ኛውን ሃገራዊ ምርጫ በሚያካሂዱ አካባቢዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ መራዘሙን አስታወቀ፡፡

በዛሬው እለት በሐረሪ፣ በሶማሌ እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ክልል ድምጽ አሰጣጥ እና ህዝበ ውሳኔ ሲከናወን ውሏል።

ነገር ግን ተጨማሪ የድምጽ መስጫ ሰአት የሚያስፈልጋቸው ምርጫ ክልሎች በመገኘታቸው እና ድምጻቸውን መስጠት የሚፈልጉ ዜጎች እድሉን እንዳያጡ በማሰብ በአዋጅ 1162/ 2011 አንቀፅ 49 (4) መሰረት በሚከተሉት ቦታዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ መራዘሙን ቦርዱ አሳውቋል።

1. በሐረሪ ክልል በሚገኙ ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች
2. ከሐረሪ ክልል ውጪ ለሐረሪ ክልል የሚመርጡ ምርጫ ጣቢያዎች
3. ሕዝበውሳኔ በሚካሄድባቸው ሁሉም የምርጫ ክልሎች (ህዝበውሳኔን ለብቻ ለሚያካሂዱ እንዲሁም ህዝበውሳኔን እና ምርጫን ለሚያካሂዱ በሙሉ)

አስፈጻሚዎች ከላይ ከተጠቀሱት ቦታዎች ውጪ ባሉ ቦታዎች 12 ሰዓት ሲሞላ ሰልፍ ላይ ያሉ መራጮችን በማስተናገድ ምርጫውን እንዲያጠናቅቁ እንዲሁም 12 ሰዓት ላይ መራጮችን አስተናግደው ያጠናቀቁ ጣቢያዎች በህጉ መሰረት ታዛቢዎች በተገኙበት ቆጠራ እንዲጀምሩ ቦርዱ ያሳስባል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.