በሶማሌ ክልል በሁሉም የምርጫ ክልሎች የድምፅ አሰጣጥ ተጠናቋል – ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በሶማሌ ክልል በሁሉም የምርጫ ክልሎች የድምፅ አሰጣጥ መጠናቀቁን ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሊቀ መንበር ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አስታወቁ፡፡
የህዝበ ውሳኔ ከሚሰጥባቸው ምርጫ ክልሎች ውጭ በደቡብ ክልል በአብዛኛው ድምፅ ተሰጥቶ መጠናቀቁን የገለጹት ሰብሳቢዋ÷ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ መሆኑን የቦርዱ ሊቀመንበር ተናግረዋል፡፡
በሶማሌ ክልል ሁለት አካባቢዎች የግል ተወዳዳሪዎችና በመስቃንና ማረቆ አካባቢ ለቦርዱ ከተወዳዳሪዎች ቅሬታ ደርሷል ብለዋል፡፡
በፓርቲዎች ግን በድምፅ አሰጣጡ ላይ ቅሬታ እንዳልቀረበም አክለዋል፡፡
አነስተኛ የአቅርቦት ችግር በተፈጠረባቸው አካባቢዎችም ፈጥኖ የማስተካከል ስራ እንደተሰራ ወይዘሪት ብርቱካን አንስተዋል፡፡
በሶማሌ፣ በደቡብ ክልል ህዝበ ውሳኔ በማይከድባቸው አካባቢዎች ቆጠራ እንደተጀመረም ጠቅሰዋል፡፡
ሆኖም የመብራት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ነገ ቆጠራ ይካሄዳል፡፡
በአፈወርቅ እያዩና ፀጋዬ ወንደወሰን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!