Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራን የማጽዳት ሥራ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በነገው ዕለት ለሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ስፍራ የጽዳት ዘመቻ ተከናወነ።
የጽዳት ሥራው በአዲስ አበባ ከተማ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በቅንጅት የተካሄደ ነው፡፡
በጽዳት መርሐግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በጎፈቃደኛ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል መባሉን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.