በፊንፊኔ ዙሪያ በአቃቂ ወረዳ በ350 ሄክታር መሬት የመስኖ ልማት ስራ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ ገመዳ ቀበሌ 350 ሄክታር መሬት የመስኖ ልማት ስራ ተጀምሯል።
በዛሬው እለት በልዩ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የመስኖ ልማት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን፥ በልዩ ዞኑ 18 ሺህ 100 ሄክታር መሬት በዘር ይሸፈናል ተብሏል።
ከዚህ ውስጥ 2 ሺህ 700 ሄክታር በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆኑ ነው የተነገረው።
ከዚህ ቀደም በተደረገ የመስኖ ልማት ከአንድ ሄክታር 105 ኩንታል ምርት መገኙቱን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ገልጸዋል፡፡
በዘቢብ ተክላይ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!