የ15 ዓመታት የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታን እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ የ15 ዓመታት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታን እውን ለማድረግ የጤና ኬላዎችንና ጤና ጣቢያዎችን ልየታ እየተሰራ መሆኑን አስታወቁ።
ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ÷ ሚኒስቴሩ ከባለ ድርሻ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር- ከጂኦስፓሻል ኢንፎርሜሽን ኢንስቲቲዩት እና ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
እስካሁን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የ11 ሺህ 103 ጤና ኬላዎችና የ3 ሺህ 532 ጤና ጣቢያዎች ልየታ መሰራቱን ጠቅሰው፥ በቀጣይም ሆስፒታሎችን ጨምሮ የሁሉም ተቋማት ልየታ ይከናወናል ብለዋል።
የተጀመረውን ትብብር በማጠናከርም የጤና የመረጃ ስርዓቱን ለማዘመን እና የጋራ ስራውን ለመገምገም ያለመ ውይይት መደረጉንም አስታውቀዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!