በኦሮሚያ ክልል ተጥሎ የነበረው የምሽት እንቅስቃሴ ገደብ ለጊዜው ተነሳ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በዜጎችና ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የምሽት እንቅስቃሴ ገደብ ለጊዜው መነሳቱን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ወይዘሮ አዱኛ አሕመድ አስታወቁ፡፡
ከህዳር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ከምሽት 3 ሰዓት እስከ ንጋት 11:30 ዜጎች እና ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ የሚያደርግ አዋጅ ተግባራዊ ተደርጎ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ያነሱት ጠቅላይ ዐቃቤ ህጓ፥ የክልሉን እና አገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳይጎዳ ከግምት በማስገባት ይህ ውሳኔ ዳግም ተላልፏል ብለዋል።
በቀጣይ ሁኔታዎች እየታዩ አዋጁ እንደገና በመላው ክልሉ እንዲሁም እንደየ አከባቢዎች ሁኔታ ሊታይ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
የእንቅስቃሴ ገደቡ ለጊዜው ቢነሳም÷ አስፈላጊው ፍተሻ በተለያዩ የፀጥታ አካላት እና ህዝባዊ አደረጃጀት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተዋል።
በአፈወርቅ አለሙ እና ምናለ ገበየሁ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!